Want to create interactive content? It’s easy in Genially!

Get started free

Breathe Better at Home (Amharic)

Delete - Climate & Health

Created on December 15, 2023

Start designing with a free template

Discover more than 1500 professional designs like these:

Vision Board

SWOT Challenge: Classify Key Factors

Explainer Video: Keys to Effective Communication

Explainer Video: AI for Companies

Corporate CV

Flow Presentation

Geographical Challenge: Drag to the map

Transcript

የቤት ውስጥ አየር ጥራት(IAQ)

“አንድ አማካይ ሰው 90% የሚሆነውን ጊዜ በቤት ውስጥ እንደሚያሳልፍ እና በቤት ውስጥ ያለው አየር ውጭ ካለው አየር ከ2-5 እጥፍ የከፋ እንደሚሆን ያውቃሉ?”

Iየቤት ውስጥ አየር ጥራት (IAQ) በቤት ውስጥ ያለውን የአየር ሁኔታ እና የአየሩ ሁኔታ ጤናችን ላይ እና ደህንነታችንን ላይ ምን አይነት ተጽእኖ እንደሚያመጣ ይገልጻል። ምክያቱም አየር ቅርጽ የሌለው እና ቀለም የሌለው ስለሆነ፣ የቤት ውስጥ የአየር ጥራት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ የተለመዱ ነገሮችን እና እንቅስቃሴዎችን ማወቅ ጤናዎትን ሊጎዱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቆጣጠር እና በቤትዎ ውስጥ ያሉ የብክለት ምንጮችን ለመቀነስ የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ይህ የመረጃ ምንጭ የቤት ውስጥ የአየር ብክለት ከየት እንደሚመጣ እና በቤትዎ ውስጥ በተሻለ ሁኔታ ለመተንፈስ የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ያሳያል።
Iመመሪያዎች

ይህ በቤትዎ ውስጥ ያለውን የቤት ውስጥ አየር ጥራት ለማሻሻል የሚረዳ ትምህርታዊ በራሪ ወረቀት ነው። በግልባጩ ላይ ያሉ ምስሎች በቤት ውስጥ የተደበቁ የአየር ብክለት ምንጮች በጤናችን ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድሩ ያሳያሉ። በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥ የአየር ብክለትን ለመቀነስ የቀረቡትን መፍትሄዎች ለማየት የታጠፉትን ምስሎች ይክፈቱ።

እነዚህን ምልክቶች በመላው ገፅ ውስጥ ይፈልጉ። የእርስዎን የቤት ውስጥ የአየር ጥራት ማሻሻያ መንገዶች ላይ ተጨማሪመረጃ ለማግኘት በመዳፊትዎ ምልክቶቹ ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

ጥሩ የቤት ውስጥ የአየር ጥራት ያለው ክፍል ለማየት በመዳፊትዎ ምልክቱ ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

የብርቱካን ምልክቶች በቤት ውስጥ ያለውን የአየር ብክለት ቅራጮች (PM) ምንጮችን ያመለክታሉ።

የሐምራዊው ምልክቶች ተለዋዋጭ የተፈጥሮ ውሁድ ( VOC) የቤት ውስጥ የአየር ብክለት ምንጮችን ያመለክታሉ።

የቢጫ ምልክቶች በቤት ውስጥ የሽታ ምንጭ መኖሩን ያመለክታሉ።

የቤት ውስጥ አየር ለቤት ውስጥ አየር ብክለት አስተዋጽኦ በሚያደርጉ ቅንጣቶች የተሞላ እና ውጭ ካለው አየር የከፋ ሊሆን ይችላል።

እንደ HEPA ያሉ ሜካኒካል የአየር ማጣሪያዎችን መጠቀም በአየር ውስጥ የሚኖሩትን ቅንጣቶች እስከ 99% ድረስ ለመቀነስ የረዳሉ።

የደካማ አየር ጥራት የጤና ተጽእኖዎች

ደካማ የቤት ውስጥ የአየር ጥራት የአጭር እና የረጅም ጊዜ የጤና ሁኔታዎች ሊያስከትል ይችላል። በተጨማሪም፣ ደካማ የቤት ውስጥ አየር ጥራት ቀደም ሲል የነበረን የጤና እክል ሊያባብስ ይችላል:: በጣም ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ህጻናት እና ልጆች፣ እርጉዝ ሴቶች፣ 65 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች፣ እና ቀደም ሲል የነበረ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ።

የደካማ የቤት ውስጥ የአየር ጥራት ሁለት ዋና ምንጮች

“አቧራ” ቅንጣት ንጥረ-ነገር (PM) PM በተለምዶ ከአቧራ ጋር የተቆራኘ ነው እናም ከቤት እንስሳት ፀጉር ወይም የቆዳ ቅርፋት፣ ከአበባ ብናኝ፣ ከምንጣፎች፣ ከቤት እቃዎች መሸፈኛ፣ እንደ ቫኩም ከማድረግ፣ ቤትን ከመጥረግ እና የሲጋራ ጭስ ካሉ ተግባራት ሊመጣ ይችላል።

የደካማ የቤት ውስጥ የአየር ጥራት ሁለት ዋና ምንጮች

“ኬሚካሎች” ተለዋዋጭ ኦርጋኒክ ንጥረ-ነገሮች (VOCs) VOCs ብዙውን ጊዜ እቤት ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውሉ ኬሚካሎች ጋር የተቆራኙ ናቸው እናም ከጽዳት ምርቶች፣ ከውበት ምርቶች (ለምሳሌ የፀጉር ስፕሬይ እና ሜካፕ ማስለቀቂያ)፣ ምግብ ከማብሰል (ለምሳሌ የጋዝ ምድጃዎች፣ የምግብ ዘይት፣ እንደ ቴፍሎን ያሉ የማያጣብቁ መጥበሻዎች በመጠቀም፣ እና ምግብን በመጥበስ)፣ የቤት ውስት መአዛ እና ሌሎች እንደ ሻማ ያሉ ጥሩ መዓዛ ያላቸው ምርቶች፣ እና የግንባታ እቃዎች (ለምሳሌ ሙጫ፣ ቀለም፣ ቅንጣት ሰሌዳ (ጣውላዎች) እና ኮምፖንሳቶ) ጋር ተያይዘው ሊመጡ ይችላሉ።

አሁን በቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ ምን ምክንያቶች የቤት ውስጥ የአየር ጥራት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ እንመረምራለን ።
የቤት ውስጥ አየር ጥራትን ማሻሻል ከቤት ውጪ ይጀምራል

ንጹህ እና የውጭ አየር ወደ ቤትዎ ማምጣት የቤት ውስጥ የአየር ብክለትን መጠን ለመቀነስ አንዱ መንገድ ነው ፡ ነገር ግን ከቤት ውጭ ባለው አየር ላይ ብቻ መተማመን የእርስዎን እና የቤተሰብዎን ጤና ሙሉ በሙሉ ለመጠበቅ በቂ ላይሆን ይችላል፣ በተለይም የውጪ አየር የተበከለ ከሆነ።

በመጸዳጃ ቤት ውስጥ የአየር ጥራትን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ለማየት በሰማያዊ ምልክቶች ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

የአየር ብክለት በሚወገድበት ጊዜ መታጠቢያ ቤቱ ምን እንደሚመስል ለማየት ሮዝ መልክቱን ጠቅ ያድርጉ።

በመኝታ ክፍሉ ውስጥ ያለውን የአየር ጥራት እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ለማየት በሰማያዊ ምልክቶች ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

የአየር ብክለት በሚወገድበት ጊዜ መኝታ ክፍሉ ምን እንደሚመስል ለማየት ሮዝ ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ።

በመጫወቻ ክፍል ውስጥ የአየር ጥራትን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ለማየት በሰማያዊ ምልክቶች ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

የአየር ብክለት በሚወገድበት ጊዜ የመጫወቻ ክፍሉ ምን እንደሚመስል ለማየት ሮዝ ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ።

የመግቢያውን መንገድ የአየር ጥራትን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ለማየት በሰማያዊ ምልክቶች ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

የአየር ብክለት በሚወገድበት ጊዜ የመግቢያ መንገዱ ምን እንደሚመስል ለማየት ሮዝ ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ።

ሳሎን ውስጥ የአየር ጥራትን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ለማየት በሰማያዊ ምልክቶች ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

የአየር ብክለት በሚወገድበት ጊዜ ሳሎን ምን እንደሚመስል ለማየት ሮዝ ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ።

በእቃ ቤት ውስጥ ያለውን የአየር ጥራት እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ለማየት በሰማያዊ ምልክቶች ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

የአየር ብክለት በሚወገድበት ጊዜ የምግብ ቤቱ ምን እንደሚመስል ለማየት የሮዝ ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ።

የምድር ቤት ውስጥ ያለውን የአየር ጥራት እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ለማየት የሰማያዊ ምልክቶች ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

የአየር ብክለት በሚወገድበት ጊዜ ምድር ቤቱ ምን እንደሚመስል ለማየት የሮዝ ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ።

በልብስ ማጠቢያ ክፍል ውስጥ የአየር ጥራትን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ለማየት በሰማያዊ ምልክቶች ላይ የኮምፒውተር ቀስትዎን ያሳርፉ።

የአየር ብክለት በሚወገድበት ጊዜ የልብስ ማጠቢያ ክፍሉ ምን እንደሚመስል ለማየት የሮዝ ምልክቱን ጠቅ ያድርጉ።

ከቤትዎ ውጭ ያሉ ነገሮች ወደ ቤት ውስጥ ለሚመጣ ደካማ የአየር ጥራት አስተዋፅዖ ያደርጋሉ

የውጪ አየር ጥራት መጥፎ በሚሆንበት ጊዜ የሚከተሉትን እርምጃዎች ለመውሰድ ግምት ውስጥ ያስገቡ።

  • መስኮቶችን ይዝጉ
  • ተንቀሳቃሽ የአየር ማጣሪያ መሳሪያን ይጠቀሙ (እንደ HEPA የአየር ማጣሪያ፣ ወይም እራሶት የሚገጣጥሙትን የአየር ማጣሪያ ሳጥን ፋን)
  • የአየር ማቀዝቀዣ ዘዴ ካለዎት የአየር ማቀዝቀዣዎን ማጣሪያ ወደ የአየር ማጣሪያ አነስተኛ የውጤታማነት ሪፖርት ዋጋው (MERVው) ከ MERV-13 ወይም ከዚያ በላይ የሆነውን ይምረጡ እና የተበከለውን የውጭ አየር ከቤትዎ ውስጥ እንዳይገባ ለማድረግ የአየር ማቀዝቀዣዎን እንደገና እሚዘዋወርበትን ሁኔታ ላይ ያድርጉት

ይህ ፕሮጀክት ሊሳካ የቻለው ከሕዝብ ጤና - የሲያትል እና ኪንግ ካውንቲ የአየር ንብረት፤ እና የጤና ፍትሃዊነት ተነሳሽነት እና የካውንቲ እና የከተማ ጤና ባለስልጣናት ብሔራዊ ማህበር (NACCHO) ከአየር ንብረት እና ጤና ፕሮግራም በበሽታ መቆጣጠሪያ ማእከል (CDC) በእርዳታ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው። ምስሎች የተነደፉት በ ዋት ኤልስ ዲዛይን ነው። በአካባቢዎ ስላለው የውጪ አየር ጥራት ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የፑጀት ሳውንድ ንፁህ አየር ኤጀንሲን ድህረ ገጽን ይጎብኙ https://www.pscleanair.gov/ (በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ ብቻ ነው)